አሸባሪው ህወሓት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው

88

ታህሳስ 10/2014 (ኢዜአ)አሸባሪው ህወሓት በሴቶች ላይ የፈጸመውን ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የሚያወግዝ ፤እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በሰልፉ ላይ 'እራሳችንን ከጥቃት ለመከላከል እንዘምታለን'፤በአፋርና አማራ ክልል በሴቶችና ህጻናት ላይ የደረሱ ጥቃቶች እና ጅምላ ጭፍጨፋ ፍትህ ይሻሉ''የሚሉ መልእክቶች እየተላለፉ ነው ።

አለም አቀፍ ተቋማት እና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እያዩ እንዳላዩ ማለፋቸውንም ኮንነዋል።

አንዳንድ ምእራባውያን አገራት ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ጫና እንዲያቆሙም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

ሰልፉ "ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም" በሚል መሪቃል ነው በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም