የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ የጭካኔ ድርጊቶችን የሚያወግዝ ሰልፍ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ የጭካኔ ድርጊቶችን የሚያወግዝ ሰልፍ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው

ድሬዳዋ ፤ ታህሳስ8/2014(ኢዜአ) አሸባሪዎቹ ህወሃትና ተላላኪው ሸኔ በንጹሃን ዜጎች እየፈጸሟቸው ያለውን የጭካኔ ድርጊቶች የሚያወግዝ ሰልፍ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹ አሸባሪዎቹ ህወሃትና ተላላኪው ሸኔ በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሱ የሚገኘውን ጭካኔ ፣ጥቃትና ጭፍጨፋ ባነገቧቸው መፈክሮች ኮንነዋል ።
አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራትና ሚዲያዎቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙና እውነትን እንዲረዱ ጠይቀዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የ"በቃ" ን ንቅናቄ ዘመቻን በይፋ መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል።
"ለኢትዮጵያ ሰላም ይስፈን !አሸባሪው ህወሃት በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃት ይብቃ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ሰልፍ ሴቶች፣ ተማሪዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
የመረሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ በሚሆነው የምድር ባቡር አደባባይ ለተሰበሰበው ሰልፈኛ የድሬደዋ አስተዳደር አመራሮች መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።