ቀጥታ፡

ቀይ ቀበሮዎቹ ለፍፃሜ ደረሱ

አዲስ አበባ ነሀሴ 18/2010 በታንዛንያ እየተካሄደ ባለው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) የማጣሪያ እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለፍጻሜ ደረሰ። ዛሬ ሩዋንዳን በግማሽ ፍጻሜ የገጠመው ብሄራዊ ቡድኑ በምንተስኖት እንድርያስ ሁለት ጎሎች በአቻ ውጤት የተለያየ ሲሆን በመለያ ምት 4 ለ 2 አሸንፎ ወደ ፍጻሜ ማለፍ ችሏል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ቀበሮዎች) እሁድ በፍፃሜው ጨዋታ የኡጋንዳ እና ታንዛንያን አሸናፊ ይገጥማል። የውድድሩ አዘጋጅ ታንዛኒያና ኡጋንዳ ከቀኑ 11 ሰዓት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ ሁለት ያደረጋቸውን ጨዋታዎችን በሙሉ በማሸነፍ ምድቡን በመሪነት አጠናቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም