ቢሮው ለአገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ 23 ሚሊዮን ብር የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

23

ታህሳስ 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለአገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች 23 ሚሊየን ብር ሚሊዮን ብር የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

በዓይነት የተደረገው ድጋፍ የስንቅ፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ አልባሳት እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ናቸው።

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ኢትዮጵያዊያን ከሀገር የሚበልጥ ነገር የለም ብለው ለሚያደርጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

“ዜጎች ለአንድ አላማ ፀንተው ከቆሙ የተሻለ ውጤት የማይገኝበት መንገድ አይኖርም” ብለዋል።

በአለም አቀፍ ደረጀ በኢትዮጵያ ላይ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ጫናዎች ለመፍጠር ቢሰሩም አልተሳካላቸውም ብለዋል።

ሀብቱ የተሰበሰበው በቢሮው ስር ከሚገኙ ኮሌጆች አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የአይሲቲ ተቋማት መሆኑን የአዲስ አበባ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሃብቱ ተናግረዋል ።

ቢሮው ለሰራዊቱ ሲያደርግ የቆየውን ሙያዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው ጠቁመዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም