በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ሊያደርግ ነው

74

ህዳር 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ "ኢትዮጵያን ለመታደግ በአንድነት እንቁም!"በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ሊያደርግ ነው።

መርሃ ግብሩ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳደግና ለማጠናከር እንዳለመም ተገልጿል።

የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ይቀላቀሉን በአንድነት ቆመን ሀብት በማሰባሰብ በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደውን የተሳሳቱ መረጃዎች ዘመቻ ለመመከት በጋራ እንቁም ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

መርሃ ግብሩ በፈረንጆቹ ታህሳስ 12 ቀን 2021 እንደሚካሄድ ኮሚቴው ገልጿል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም