ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በሲፖዚየም እየተከበረ ነው

ድሬዳዋ፤ ህዳር 29/2014(ኢዜአ) 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል "ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት "በሚል መሪ ሃሳብ በሲፖዚየም እየተከበረ ነው፡፡


በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት የሚካሄደው የበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት የተጀመረው  የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴና  የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት ነው።

እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ፣የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮችና  ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሌሎችም የፌደራልና የየክልሉ አመራሮች፣ የሁሉም የኃይማኖት ተቋማት መሪዎች ፣ባህላዊ የማህበረሰቡ መሪዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና  የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮችም ተካፋይ ናቸው ።

በሲምፖዚየሙ  ላይ  በህገ መንግስቱ መሠረታዊ ትሩፋቶችና በፌደራል ስርዓቱ መጠናከር እንዲሁም  የኢትዮጵያን ልዕልናና ብልፅግና ማረጋገጥ ኢትዮጵያውያን በህብረ ብሔራዊ አንድነት እያከናወኑ የሚገኙትን ርብርብ በሚጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም