የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች አስቸኳይ ልዩ ጉባኤ እየተካሄደ ነዉ

66

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች አስቸኳይ ልዩ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው 'ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት' በሚል መሪ ሀሳብ ነዉ እየተካሄደ የሚገኘው።

በጉባኤው ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮች እንዲሁም የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

በጉባኤው ላይ መንግስት እየወሰደ ያለዉ የሕልውና ማስከበር ዘመቻ የተገኙ ድሎች፣አፈጻጸምና በቀጣይ ዘመቻውን ወደላቀ ደረጃ ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ዉይይት ይደረጋል።

የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮቹ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጸጥታ አካላት የግዳጅ አፈጻጸም አስመልክቶ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ውይይት ያደርጋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም