በሸዋሮቢት ከተማ ለታሪክ ምስክርነት የተረፈ ንብረት የለም፤ ሙሉ በሙሉ ወድሟል

96

ህዳር 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) መድሃኒት ቤቶች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች፣ ተዘርፈዋል፤ ከዘረፋ የተረፉት ደግሞ ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ተደርገው ወድመዋል።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ የውብዳር መሀመድ የሽብር ቡድኑ ከተላላኪው ሸኔ ጋር በመተባበር ከተማዋን አውድሟታል ይላሉ።

"ሐብትና ንብረት ይተካል" የሚሉት ወይዘሮዋ ወራሪው ንጹሃንን በአደባባይ በመረሸን የጭካኔውን ጥግ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ ህወሓት ወራሪዎች መነኩሴ ሳይቀር በመድፈር ነውረኝነታቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት።

"የትግራይ ወራሪዎች አንዲትን ሴት ስምንት ሆነው በመድፈር ለሰው ልጅ አዕምሮ የሚከብድ ኢ-ሠብዓዊ ድርጊት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም