የብሔራዊ ባንክ አመራርና ሰራተኞች ደማቸውን ለሰራዊቱ፤ ሞያዊ ሃላፊነታቸውን ደግሞ ለአገሪቱ እያዋሉ ነው

57

አዲስ አበባ፤ ህዳር 23/2014 (ኢዜአ) የብሔራዊ ባንክ አመራርና ሰራተኞች ደማቸውን ለሰራዊቱ፤ ሞያዊ ሃላፊነታቸውን ደግሞ ለአገሪቱ እያዋሉ መሆኑን የብሔራዊ ባንክ አመራርና ሰራተኞች ተናገሩ።
የባንኩ ሰራተኞች በተለያየ መንገድ የፋይናንስ ስርዓቱን በማዛባት የአገርን አቅም ለማዳከም የሚጥሩ አካላትን በመከላከል ረገድ በትጋት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

የስራ ሰዓትን በማክበር፣ የመንግስትን ሚስጢር በመጠበቅና የፋይናንስ ወንጀሎች ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከሌላው ጊዜ  በተለየ መልኩ በልዩ ትኩረት እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለአገር መከላከያ ሰራዊት ለሶስተኛ ጊዜ ደማቸውን የለገሱ ሲሆን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እየተዋደቀ ላለው ጀግናው ሰራዊታችን የደም ልገሳ በማድረጋችን ተደስተናል ብለዋል።

የባንኩ ሰራተኞች ደማቸውን ለሰራዊቱ፤ በሞያዊ ሃላፊነታቸው ደግሞ ለኢትዮጵያ ስኬት በአግባቡ እያዋሉ መሆኑን ገልጸዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ፤ ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ ከመሆን ባሻገር ጀግናውን ሰራዊት መደገፍና የደም ልገሳ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የባንኩ ሰራተኞች ደም ከመለገስ ባለፈ ከቀያችው ለተፈናቀሉ ዜጎች የቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው።

የአገር ህልውና የማስጠበቅ ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሰራተኞቹ በየወሩ ከደሞዛቸው ላይ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም