ከጓደኛዬ ለይተው ወሰዱኝ፤ ራሴን በማላውቀው ቤት ወድቄ አገኘሁት፤ በከተማው ምን ሲካሄድ እንደነበርም አላውቅም

193

ህዳር 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) "ከጓደኛዬ ለይተው ወሰዱኝ፤ ራሴን ከማላውቀው ቤት ወድቄ አገኘሁት፤ በከተማው ምን ሲካሄድ እንደነበርም አላውቅም"--በመዘዞ ከተማ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን መደፈር የደረሰባት እህት፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች የፈጸመውን የንጹሃን ግድያ፣ መድፈር፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ መዘዞ ከተማም ደግሞታል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ህመምተኛ ሴትን አስገድደው በመድፈር የአረመኔነት ግብራቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡

የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው ሴት "ከጓደኛዬ ለይተው ወሰዱኝ፤ ራሴን ከማላውቀው ቤት ወድቄ አገኘሁት፣ በከተማው ምን ሲካሄድ እንደነበር አላውቅም፤ ከቀናት በኋላ ነው ወጥቼ መንቀሳቀስ የቻልኩት" ስትል ተናግራለች፡፡

የሽብር ቡድኑ በጣርማበር ወረዳ መዘዞ ከተማ በቆየባቸው ቀናት ንጹሃንን በግፍ ጨፍጭፏል፤ እንስሳት እያረደ በልቷል፤ እንስሳትን ገድሏል፤ በከተማዋ ያሉ ሱቆችን ዘርፎ የቀረውን ጥቅም ላይ እንዳይውል አድርጎ አውድሟል።

የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ አባላትን ምት መቋቋም ተስኖት ሲፈረጥጥ ዛሬም እንደትናንቱ ሁሉ ንጹሃንን በመግደል እንዲሁም የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶችን በማውደም አረመኔነቱን በተግባር አሳይቷል።_

አካባቢህን ጠብቅ፣ _

ወደ ግንባር ዝመት፣_

መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም