ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ270 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ በድረገጽ ተሰበሰበ

55

ህዳር 20/ 2014(ኢዜአ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በድረገጽ ከ 270 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሚውል ድረገጽ ማይ ገርድ ዶት ኮም( www.mygerd.com) ሐምሌ 18 ፤2013 ይፋ ተደርጎ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሉት አራት ወራት ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አቅማቸው በፈቀደ መጠን ርብርብ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህም በድረገጹ እስከ አሁን 1855 ለጋሾች ተሳትፈው 270 ሺህ 952 የአሜሪካን ዶላር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማሰባሰብ መቻሉን ገልጿል።

ከፍተኛ ንቅናቄ በመፍጠር ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራውን ከመሩት መካከል ታዋቂ ግለሰቦችና ተቋማት እንደሚገኙበትም በመረጃው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም