ቀጥታ፡

የምዕራባውያን አገራት በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚቃወም ሰልፍ በፕሪቶሪያ እየተካሄደ ነው

ህዳር 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የምዕራባውያን አገራት በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚቃወም ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጁት የተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ እና የአፍሪካ ዳያስፖራ ፎረም ናቸው።

ሰልፈኞቹ በፕሪቶሪያ ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን፤ ለኤምባሲውም ደብዳቤ አስገብተዋል።

በተመሳሳይም ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአውሮፓ ሕብረት መስሪያ ቤት ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙና ደብዳቤ እንደሚያስገቡ ተገልጿል።

በሰልፉ ላይ በደቡብ አፍሪካ ዘጠኝ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን፣ ደቡብ አፍሪካውያንን ጨምሮ በአገሪቷ የሚኖሩ የተለያዩ አፍሪካ አገራት ዜጎችና የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኞች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ከሰልፉ አስተባባሪዎች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሰልፉ ላይ ምዕራባውያን አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ላይ ለመጫን የሚፈልጉትን ዘመናዊ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ የሚቃወሙ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ የሚያሳዩበት እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ከሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው የአፍሪካ ዳያስፖራ ፎረም ከ35 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ዳያስፖራዎችን ያቀፈ ድርጅት ነው።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣ _

ወደ ግንባር ዝመት፣_ መ

ከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም