አዲስ አበባ እንደተለመደው ሰላም ናት፣ይልቁንም የቦሌ አየር መንገድ ከአሜሪካ በመጡ ተጓዦች ሙሉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ እንደተለመደው ሰላም ናት፣ይልቁንም የቦሌ አየር መንገድ ከአሜሪካ በመጡ ተጓዦች ሙሉ ነው
ህዳር 20 /2014(ኢዜአ) የአሜሪካና የምዕራባውን ተቋማት ከሚያወጡት መግለጫ በተቃራኒ አዲስ አበባ እንደተለመደው ሰላም ናት ፣ ይልቁንም የቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ከአሜሪካ በመጡ ተጓዦች ተሞልቷል ሲል የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኙ ላውረንስ ፍሪማን አመለከተ።
ከ30 ዓመታት በላይ በአፍሪካ የፖሊሲና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ምርምር በማድረግ የሚታወቀው ላውረንስ ፍሪማን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ መግባቱን ገልጾ ፣ አዲስ አበባ የአሜሪካና የምዕራባውን ተቋማት ከሚያወጡት መግለጫ በተቃራኒው በተለመደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ ላይ ትገኛለች ብሏል።
በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በሙሉ አቅም አገልግሎት እየሰጡ ነው ሲልም አመልክቷል።
ይልቁንም የቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከአሜሪካ በመጡ በርካታ ተጓዦች መሞላቱን ነው የገለጸው።
“ውሸትና ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ይቁም እዚህ አፍጋኒስታን የለችም የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ የሚካሄደው እንቅስቃሴም ይቁም” ሲል አስታውቋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!