ዳያስፖራው በኦንላይን መተግበሪያ ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበው ገንዘብ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
ዳያስፖራው በኦንላይን መተግበሪያ ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበው ገንዘብ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደረሰ
ህዳር 18/2014 (ኢዜአ) ዳያስፖራው በ'eyezonethiopia.com' መተግበሪያ አማካኝነት በሃገር ቤት አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበው ገንዘብ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው ከቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ባለማውና ባስተዋወቀው እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ መስመሩን ባመቻቸው መተግበሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰቡን ገልጿል።
ይህም ዳያስፖራው ምቹ ሁኔታ እስከተፈጠረለት ድረስ ሃገሩን ለመርዳት ያለውን ዝግጁነትና ዕምቅ አቅሙን ማሳየቱን መረጃው ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በድጋፉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋና ማቅረቡን የገለጸው መረጃው፣ ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል የሃገር አለኝታነቱን ዳግም እንዲያረጋግጥ ጥሪ ማቅረቡን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢህን ጠብቅ
ወደ ግንባር ዝመት
መከላከያን ደግፍ