በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመራው መላው የጸጥታ ሃይል ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው

91

ህዳር 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው መላው የጸጥታ ሃይል ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዳመለከተው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መላውን የጸጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የህልውና ዘመቻውን ከዳር ለማድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።

“በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ያወጣ ሲሆን ወደፊት በመገሥገሥ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው” ብሏል።

የጸጥታ ሃይሉ በአፋር ክልል፣ በጭፍራ ግንባርም ጪፍቱን፣ የጭፍራ ከተማንና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገሥገሥ ላይ ነው።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም