ኢትዮጵያ ፈርሳ "የፈረሰ ሥነ ልቦና እና የፈረሰ ነጻነት ይዤ ከምኖር ሞቴን እመርጣለሁ"

119

ህዳር 15/2014 (ኢዜአ) ሠላሟና ነፃነቷ የተረጋገጠ፤ ሉዓላዊት ኢትዮጵያን ለማስቀጠልና ለትውልድም ለማስተላለፍ መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ወጣቶች ተናገሩ።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች ጠቅላይ ሚኒስትር  አቢይ አህመድ " ኢትዮጵያ  የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን" በማለት ወደ ግንባር መዝመታቸውን ያነሱት ወጣቶቹ የእርሳቸውን ፈለግ እንደሚከተሉ ገልጸዋል።

ወጣት ኤርሚያስ ብርሃን እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር በመዝመት የአባቶቻችንን ታሪክ ደግመውታል፤ በዚህም እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንም አስመስክረዋል ብሏል።

"እኔ ማለት አገር ነኝ፤ አገር ስትፈርስ የሚፈርሰው የእኔ ነጻነት ነው" ያለው ወጣቱ "የፈረሰ ስነ ልቦና፣ የፈረሰ ነጻነት ይዤ ከምኖር ብሞት እመርጣለሁ" ሲል ተናግሯል።

"የጥንት አባቶቻችን ዘማቾችን ብቻ አልነበረም የሚልኩት ራሳቸውም ይዘምቱ ነበር ታዲያ ኢትዮጵያ ሰው እንዳላጣች አይቼበታለሁ፤ ስለዚህ አገር አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መሪውን ተከትሎ መዝመት አለበት ይሄ የስሜታዊነት ቅስቀሳ አይደለም የብስለት ጉዳይ ነው ያለ ሀገር አይኖርም ነው። እኔ ማለት አገር ነኝ እኔ ማለት ኢትዮጵያ ነኝ ኢትዮጵያ ስትፈርስ የሚፈርሰው የእኔ ስነ ልቦና ነው የሚፈርሰው የእኔ ነጻነት ነው የፈረሰ ስነ ልቦና የፈረሰ ነጻነት፣ የተማረከ ነፃነት ይዤ ከምኖር ብሞት እመርጣለሁ እርሳቸውም ይህን ሲወስኑ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አይቼበታለሁ ማንም ሰው መኖር ከፈለገ የሚኖርበት አገር ያስፈልገዋል እና ወጣቱ እሱ ሞቶ ለልጆቹ ነጻ አገር ማሳለፍ ከቻለ በትልቁ መኖር በብዙ መኖር ነው"

ወጣት መስፍን ጌታቸው ደግሞ ለአገሬ መስዋዕትነት የምከፍለው "አገሬ መኖሪያዬ፣ የመጨረሻዬና ለልጄም የማወርሳት ሐብቴ ስለሆነች ነው" ብሏል።

"እንግዲህመሪ ከዘመተ መሪ ከፊት ከቀደመ ሌላው ዝብ የብረተሰብ ክፍል መከተል መቻል አለበት እስከወያኛው ሄዶ መስዋትነት መክፈል መቻል አለበት በነገራችን ላይ እኔ ለአገሬና ለልጄ መስዋትነት የምከፍለው አገሬ የመጨረሻዬ የትም መሄድ የማልችልበት መኖሪያዬ የኖርኩባት ብዙ ነገር ያሳለፍኩባት ነች ለልጄም የማወርሰው አገር ነው ሌላ ሀብት የለንም ኖርማሊ እና አገር ካላወረስን ቀጣይ ትውልድ ደግሞ ከዚህ ከጠላት ጠብቀን አገራችንን ማስተላለፍ ካልቻልን ችግር ነው"

ወጣቱ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አይነት ቆራጥ ውሳኔ ሊወስን ይገባል ያለው ደግሞ ወጣት አብዮት ሰለሞን ነው።

"መሪ ስትሆን ሁሉም ነገር ቀዳሚ ነው እና ወጣቱም በእንደዚህ አይነቱ ቆራጥ ሳብ ቆራጥ ውሳኔዎችን መወሰን ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም ለወጣቱ የሚያስተላልፈው ትልቅ መልክት ነው ብዬ እወስዳለሁ ጠቅላይ ሚስትሩ የወሰኑት ውሳኔ ብዙ ሰዎችን ያነሳሳል የሚል ግምትም አለኝ"

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም