ጠቅላይ ሚኒስትሩን አርአያ በማድረግ የህልውና ዘመቻውን እንቀላቀላለን

14

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ኢህአፓ/ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊና የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርዎች አመራር መጋቢብሉይ አብረሀም ሃይማኖት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አርአያ በማድረግ የህልውና ዘመቻውን እንደሚቀላቀሉ ተናገሩ ።

"ለአፍሪካውያን ተምሳሌትና ለአለም ህዝብ አይደፈሬነታችነን ለማሳየት እዘምታለሁ" ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቆራጥነት ስንጠብቀው የነበረ ነው ያሉት ።

ወቅቱ የህልውና ዘመቻውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ወሳኝ ጊዜ መሆኑን ገልጸው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ተምሳሌታዊ ተግባር ሊከተል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ አሻንጉሊት መንግስት ለመመስረት ለቋመጡ ትምህርት ለመስጠት ጊዜው አሁን መሆኑንም አመላክተዋል።

በድልም ተመልሰን የኢትዮጵያን ህዝብ ሰላምና፣ ለአለማቀፍ ህብረተሰብ አይበገሬነታችንን እናሳያለን ብለዋል።

እንደ ፓርቲም ኢህአፓ የያዘው አቋም ኢትዮጵያን ማዳን ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም