ከዳያስፖራ አባላት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ - ኢዜአ አማርኛ
ከዳያስፖራ አባላት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ
ህዳር 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ6 ሺህ 269 የዳያሰፖራ አባላት እስካሁን በኦንላይን ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የገንዘቡ ድጋፍ በ'eyezonethiopia.com' መተግበሪያ አማካኝነት የተሰበሰበ ነው።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ከሁለት ሳምንት በፊት ባስተዋወቀውና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ መስመሩን ባመቻቸው መተግበሪያ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በድጋፉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናውን አቅርቧል።
የዲያስፖራ ኤጀንሲ ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
-አካባቢህን ጠብቅ
_ ወደ ግንባር ዝመት
_ መከላከያን ደግፍ