ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደረጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ በአሜሪካ አትላንታ ተካሄደ

97

ደህዳር 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደረጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወመው ዓለም አቀፍ ሰልፍ አካል የሆነው ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ አትላንታ ተካሄደ።

በሰልፉ ላይ አሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ያልተገባ ጫና እንዲያቆሙ የሚጠይቁ መፈክሮች ተሰምተዋል።

‘የአፍሪካን ችግሮች ለአፍሪካውያን፣ ይበቃል ስንል ይበቃል ነው፣ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ፈጽሞ ለአገራት መፍትሄ ሆኖ አያውቅም፣ ችግሮቻችንን እኛው እንፈታቸዋለን፣ የሀሰት ዘገባችሁን አቁሙ’ የሚሉና ሌሎች ጣልቃገብነትና ጫናዎችን የሚያወግዙ ድምጾች በሰልፉ ላይ ተስተጋብተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም