ቀጥታ፡

ከኢትዮጵያ ተሰርቀው የወጡ አስራ ሶስት የተለያዩ ቅርሶች ተመለሱ

ህዳር 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ ተሰርቀው የወጡ አስራ ሶስት የተለያዩ ቅርሶች ተመለሱ፡፡

ቅርሶቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ነው የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የተናገሩት፡፡የእጅ መስቀል፣ ዘውድ፣ የጸሎት መጽሃፍት፣ መጠጫዎች እና የተለያዩ ሃይማኖታዊ ቅርሶች ከተመለሱት መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ቅርሶቹን ለማስመለስ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል ነው ያሉት፡፡

ቅርሶቹ በአግባቡ ተጠብቀው ለጎብኝዎች ክፍት እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ለጥናትና ምርምር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸውም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም