ቀጥታ፡

የውጪ ሃይሎች የኢትዮጵያን እድገት በተለያዩ ጫናዎች ማዳከም ይሻሉ

ህዳር 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በማልማት ለማደግ የምታደርገውን ጥረት በጦርነት ለማሰናከልና ለማዳከም የሚሰሩ ሃይሎች እንዳሉ የዌክአፕ አፍሪካ ሾው አዘጋጅ ዶክተር ሙምቢ ሲራካ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ሁሉን አቀፍ ጫና ከጦርነቱም ቀድሞ ሲሰራበት መቆየቱን የተናገሩት ዶክተሯ፤ በተለይም የህዳሴ ግድብን ለማሰናከል የተለያዩ ጫናዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

“ግብፅ ከፈለገች ግድቡን ታፈነዳዋለች” መባሉንም በአብነት አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ አለም አቀፍ ሚዲያዎችና የእርዳታ ድርጅቶች የተቀናጀ ዘመቻ ስለመክፈታቸው አስረጂ የሚሆነው አንድ አይነት ቋንቋ መናገራቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

“ኢትዮጵያውያን ይህንን ለመመከት በውስጥም በውጪም አይበገሬነታቸውን ማሳየታቸው መልካም ነው” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ አቅም ለመስራት መወሰኗ አለም አቀፍ ጫናውን ለመቋቋም እንዳገዛት ገልፀው፤ በዲፕሎማሲው አጋር የሆኗት ራሽያና ቻይናም በኢትዮጵያ ጉዳይ የአለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን አቅም ለመቀነስ እየረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ እውነታውን የያዙ ትክክለኛ መረጃዎችን ብቻ ማጋራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፤ “በአለም አቀፍ ሚዲያ የሚሰሩ የተሳሳቱ ዜናዎችን ማጋራት ጠላትን የመጥቀም ድርጊት ነው” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳከም በግልፅም በስውርም አሸባሪውን ህወሃት የሚደግፉ እንዳሉ ጠቅሰው፤ “በጦርነቱ የውጭ ቅጥረኞች መታየታቸው ለዚህ ተግባር አስረጂ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም አገር እና የእድገት ምሰሶም በመሆኗ ልትደገፍ እና ልትጠበቅ ይገባል” ያሉት ዶክተር ሙምቢ ከታሰበላት ወጥመድ ለመውጣት የህዝብ አንድነቷን ማጠናከር እንዳለባት አስገንዝበዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም