ቀጥታ፡

ይህ ወቅት ታሪክ የምንሰራበት ነው

ህዳር 8/2014 (ኢዜአ) ይህ ወቅት ታሪክ የምንናገርበት ሳይሆን ታሪክ የምንሰራበት ወቅት ነው ሲሉ በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የሚያሰለጥኑ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ገለጹ።

የቀድሞ ሰራዊት አባላት እና የ35ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ‘’ሀገራችንን ከአሸባሪው ወራሪ ሃይል ለመታደግ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ‘’ብለዋል።

ሻ/ል ፈለቀ ደበሌ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት 102ኛ ክፍል ጦር አየር ወለድ አባል ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የመግስትን ጥሪ በመቀበል በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሻምበል አዛዥ በመሆን የድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

ሻ/ል ፈለቀ ግፍና በደል ደርሶብን ከሰራዊቱ ብንገለልም በሀገር ድርድር ስለሌለ ዛሬም ሀገራችንን ከባንዳዎች ለማዳን ወራሪውን ሃይል ለመፋለም ዝግጁ ነኝ ብለዋል::

ምክትል መቶ አለቃ ቀለምወርቅ ድረስ በበኩላቸው ፣ ሳይወዱ በግድ ከሚወዱት የውትድርና ሙያ መሰናበታቸውን አውስተው ፣ የእናት ሀገር ጥሪ ተቀብለው ወደ ሙያቸው በመመለሳቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ሀገር ወደ ነበረችበት ሰላም ለመመለስ ማንኛውንም መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ምልምል ሰልጣኝ ሮቤል መለስ እና ምልምል ሰልጣኝ ገነነ ፍቃዱ በሰጡት አስተያየት ፣የሚሰጣቸውን ስልጠና በላቀ ውጤት በማጠናቀቅ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በጀግንነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ::

-አካባቢዎን ይጠብቁ!

-ወደ ግንባር ይዝመቱ!

-መከላከያን ይደግፉ!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም