ወረኢሉን ለመቆጣጠር አስቦ ኃይሉን ሲያሰባስብ የነበረው አሸባሪው ሕወሓት ተደመሰሰ

15

ህዳር 7/2014(ኢዜአ) ወረኢሉን ለመቆጣጠር አስቦ ኃይሉን ሲያሰባስብ የነበረው አሸባሪው ህወሓት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖና የአካባቢው ታጣቂ በጋራ በፈጸሙት ጥቃት መደምሰሱን ከግንባር የተገኙ ምንጮች ገልጸውልናል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ቡድን አባላት የተደመሰሱ ሲሆን ከፍተኛ የጁንታው አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሺዎች መማረካቸውም ታውቋል።

አሸባሪው ቡድን በዚህ ግንባር ከሕጻን እስከ ሽማግሌ ያሰለፈ ሲሆን ከተማረኩት ብዙዎቹ በየአካባቢው ያለው የሕወሓት ተዋጊ ተስፋ እየቆረጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ጀግናዎቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ወደ ፊት እየገሠገሡ መሆኑንም ነው ምንጮች ከስፍራው የሰጡን መረጃ የሚያመላክተው ።

_አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም