በዓሉን ስናከብር የአገሪቱን አንድነትና ሰላም በማስጠበቅ የተፈናቀሉ ዜጎችን መርዳት ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
በዓሉን ስናከብር የአገሪቱን አንድነትና ሰላም በማስጠበቅ የተፈናቀሉ ዜጎችን መርዳት ይገባል
አዲስ አበባ ነሀሴ 15/2010 በዓሉን ስናከብር የአገሪቱን አንድነትና ሰላም በማስጠበቅ እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጎችን በመርዳት መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይዎች ጠቅላይ ምክር ቤት ገለጸ። 1439ኛ የዒድ አል አደሃ አረፋ-በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም የኃይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና በከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በዚሁ ጊዜ የምክር ቤቱ ተወካይ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እዲሪስ እንዳሉት በዓሉን ስናከብር የአገሪቱን አንድነትና ሰላም ማስጠበቅ፣የተፈናቀሉ ዜጎችን የመርዳት፣ከሌሎች የኃይማኖት ተከታዮች ጋር በፍቅርና በመከባበር መሆን አንዳለበት ተናግረዋል። የአገራችን ሙስሊሞች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም በአገራችን ሰላምና አንድነት እንዲጠናከር የሚያደርገውን ተሳትፎ በማጠናከር የአገሪቱን የለውጥ ጊዜ መደገፍ ያስፈልጋልም ብለዋል።
በዓሉን ልዩ የሚያደርገው በተለያዩ አገራት የነበሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እየተመለሱ ያሉበት ጊዜ መሆኑ ነው ሲሉም ጠቁመዋል። የእስልምና ኃይማኖት 'ፈጣሪ የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ልህቅናና ክብር የፈጠረው መሆኑን' እና እስልምና ፍቅር፣ ሰላም፤ አንድነት መሆኑንም ጠቁመዋል። ከኃይማኖቱ አስተምህሮ ውጭ የሚፈጠሩ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ያወግዛል፣ በመሆኑም ሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነቱን በማጠናከር መሆን አለበት ብለዋል። የኢትዮጵያ ሙስሊም ተቋማዊ ለውጥ አንድነት ኮሚቴ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉን ስናከብር በፍቅር፣ በአንድነት እና በአገራዊ ለውጥ ውሰጥ መሆኑን ጠቁመው በአገራችን አሁን እየመጣ ያለውን ዘርፈ ብዙ ለውጥ ለማስቀጠል ሁሉም በአንድነት መንፈስ መደገፍ እንዳለበት አሳስበዋል። በሰላም፣በፍቅር፣ በአንድነት ልማታችንን ልናፋጥን ይገባል፣ በዚህም የእስልምና አስተምህሮ በሚፈቀደው መሰረት ወደ አንድነት መምጣት አለብን ብለዋል። እስልምና ሰላም የሚሰብክ ሃይማኖት በመሆኑ ተከታዮቹም በዚህ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል። የሃይማኖቱ ተከታዮች በአካባቢው የሚከሰቱ ችግሮችን ማውገዝ እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል። በከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ለሃይማኖቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ በማለት፣ በዓሉን ልዩ የሚያደርገው አገሪቱ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለችበት ወቅት መከበሩ ነው ብለዋል። ኢንጂነር ታከለ አክለውም ይህቺን የሁሉም ቤት የሆነችዋን አዲስ አበባ አልምተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሙስሊሙ ማህበረሰብም አገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ውሰጥ የተጀመረውን ታሳትፎ ማጠናከር አለበት በማለት ጥሪ አቅርበዋል።