አሸባሪው ህወሃት የሚሌ መስመርን እንደተመኘው ይቀራል - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪው ህወሃት የሚሌ መስመርን እንደተመኘው ይቀራል
ህዳር 7/2014 /ኢዜአ/ አሸባሪው ህወሃት የሚሌ መስመርን እንደተመኘው ይቀራል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሚሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
አሸባሪው ህወሃት በውሸት የተካነ በመሆኑ ለሚያሰራጫቸው ሀሰተኛ መረጃዎች ጆሮ እንደማይሰጡም ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡
አሻባሪው ህወሓት የኢትዮ- ጂቡቲ ዋና መንገድን ለመዝጋት አስቦ እየተንቀሳቀሰ ካለበት አቅጣጫ አንዱ የሚሌ መስመር መሆኑ ይታወቃል።
ነገር ግን የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአፋር ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ሕዝቡ በጋራ በመፋለም የአሻባሪውን ምኞት እያመከኑት መሆኑን በስፋራው ያሉ የክልሉ የፀጥታ ሀይሎችና ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
አሸባሪው ቡድን የለመደውን የውሽት ፕሮፓጋንዳ ከማናፈስ ባለፈ ምንም አይነት አቅም እንደሌለውና እየተደመሰሰ መሆኑንም ነው እነዚሁ አካላት የሚገልጹት።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የሚሌ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ አሸባሪው ህወሓት ሚሌን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት በምንም አይነት መልኩ የሚሳካ እንዳልሆነ ሊገነዘብ ይገባል ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት የሚሌ ሕዝብ አሸባሪውን መመከት የሚያስችል በቂ አቅም፣ ዝግጅትና ጉልበት እንዳለውም ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።
የሚሌና አካባቢው ነዋሪዎች በውሸት ፕሮፓጋንዳ ሳይበገር መደበኛ የእለት ከእለት ህይወቱን በሰከነ መልኩ እየመራ እንደሆነም አመልክተዋል።
የሚሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ውቲካ በበኩላቸው አሸባሪው ቡድን የሐሰት መረጃ ከማናፈስ ውጭ የሚሌን መተላለፊያ ለመዝጋት የሚያደርገው ጥረት ሕልም ሆኖ የሚቀር መሆኑን አረጋግጠዋል።
የሚሌ ከተማ በተለመደው መልኩ መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝም ገልጸዋል።