ቀጥታ፡

የኢፌዴሪ አየር ኃይል በመጀመሪያ ዙር በኤር ፓሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ

ህዳር 06 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል በመጀመሪያ ዙር በኤር ፓሊስ ኮማንዶ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ።

የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር ሎጀስቲክስ ብ/ጄ ነገራ ሌሊሳ፤ “በጀግናው ሰራዊታችንና በህዝባችን መስዋዕትነት የተደቀነብን የህልውና አደጋ እየተቀለበሰ ይገኛል” ብለዋል።

“አየር ኃይል ለምድር ኃይላችን አስተማማኝ የውጊያ ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ የጠላት ወረዳ ድረስ ዘልቆ በመግባት አሸባሪ ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል” ያሉት ጄነራል መኮንኑ፤ ተመራቂ የኤር ፖሊስ ኮማንዶ የሰራዊት አባላትም ለተቋሙ የግዳጅ አፈፃፀም ስኬታማነት ተጨማሪ አቅም መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ለቀጣይ ተልዕኮ ራሳችሁን ይበልጥ በማዘጋጀት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የስልጠናው አስተባባሪ ኮ/ል ተፈራ እሸቴ በበኩላቸው ሰልጠኞች የሚሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት መወጣት የሚያስችል ስልጠና በመውሰድ በላቀ ውጤት ማጠናቀቅ መቻላቸውን ገልፀዋል።

ከተመራቂዎች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት፣ “ስልጠናው ወደ ፊት የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ በፅናትና በቁርጠኝነት እንድንወጣ አጋዥ ነው” ማለታቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት መረጃ አመልክቷል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣ _

ወደ ግንባር ዝመት፣_

መከላከያን ደግፍ።



የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም