ቀጥታ፡

የአፍሪካ ህብረት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ አደራዳሪነት ውጤት ያመጣል

 አዲስ አበባ ህዳር 3/2014 /ኢዜአ/ የአፍሪካ ህብረት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ አደራዳሪነት  ውጤት ያመጣል በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል አፕተን።

አምባሳደሩ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተገኝተው ከሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች መክረዋል።

በዚሁ ግዜ ነው የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነትን እንደሚደግፉ የገለጹት።

በቀጣይ በአረንጓዴ ልማትን እውን በማድረግ  የዜሮ ካርበን ልቀት መጠን ግብን ለማሳካት በአፍሪካ ህብረት በኩል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ሃገራቸው ማቀዷን ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት አመታት ከ4ቢሊየን በላይ የተለያዩ አይነት ችግኞት መተከላቸውን ገልጸው ይህ ተግባር የአባይ ወንዝ ጨምሮ በሃገሪቱ ያሉ የውሃ አካላትን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የህዳሴ ግድብም ለሱዳንና ልግብፅ ያለውን ጥቅም አስረድተዋል።

 ሁለቱ ሀገራት በታዳሽ ሀይል ልማት፤ በውሃና ሳኒቴሽን፤  በአከባቢ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን  ለመመከት በሚያስችል ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን  ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም