ቀጥታ፡

ህዝበ-ሙስሊሙ ስርዓት አልበኝነትና አስነዋሪ ድርጊቶችን እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ነሃሴ 14/2010 የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ህዝበ-ሙስሊሙ ከሌሎች የሃይማኖት ተከታዮች ጋር በመሆን በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ያለውን ስርዓት አልበኝነት እና አስነዋሪ ድርጊቶች እንዲከላከል ጥሪ አቀረበ። ተቋሙ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 439ኛ የዒድ-አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል። ጉባኤው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የጤናና የአንድነት እንዲሆን ተመኝቷል። ህዝበ-ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ሃይማኖቱ በሚያስተምረው መሰረት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቀለው በተለያዩ የመጠለያዎች የሚገኙ ወገኖችን በማሰብናበማካፈል እንዲሆንም መክሯል። በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚታየው ስርዓት አልበኝነት እና በሃይማኖት የተወገዙ አስነዋሪ ድርጊቶችን ከሌሎች የሃይማኖት ተከታይ ወገኖቹ ጋር በመሆን እንዲከላከልና ሃይማኖታዊ ዕሴቶችን ጠብቆ እንዲንቀሳቀስ ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም