15ኛው ዙር "ጉሚ በለል" የውይይት መድረክ "የኦሮሞ ህዝብ ትግል እና የአሸባሪው ህወሓት ወረራ" በሚል ርዕስ እየተካሄደ ነው

64

ጥቅምት 29/2014 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የሚዘጋጀው "ጉሚ በለል" የውይይት መድረክ "የኦሮሞ ህዝብ ትግል እና የአሸባሪው ህወሓት ወረራ" በሚል ርዕስ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት አቶ ከድር ማሞ የኦሮሞ ህዝብ  ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጋር በመሆን አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማስወገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ ዓላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት አሸባሪ ቡድኑን ለማስወገድ መስራት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ለአገር አንድነትና ግንባታ ከፍተኛ ሚና እያበረከተ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

በውይይት መድረኩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

"ጉሚ በለል" በ2013 ዓ.ም መጀመሪያ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አማካኝነት የተጀመረ ሲሆን፤ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚካሄድ የውይይት መድረክ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም