በሐረሪ ክልል አሻባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል አሻባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ሐረር፣ ጥቅምት 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሐረሪ ክልል አሻባሪዎቹን ህውሃትና ሸኔን የሚያወግዝና የአገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላትን የሚደግፍ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የክልሉ ነዋሪዎች አሸባሪዎቹን ህውሃትና ሸኔን በመቃወም ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን በታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ እየገለፁ ነው።
የክልሉ የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎች፣ ተማሪዎች፣ አርሶ አደሮች፣ የመንግስት ሠራተኞች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሐረር ከተማ ዋና ዋና አደባባዮች አሸባሪና አገር አፍራሾቹን ህወሃትና ሸኔን በማውገዝ ላይ ናቸው።
ሰልፈኞቹ 'ጁንታው የኢትዮጵያ ጠላት ነው፣ ሃላፊነታችን ታሪካዊ ነው!፣ ለወራሪ ጠላት አንበረከክም፣ እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ለውጫዊ ጫና የሚንበረከክ ማንነት የለንም!!፣ ኢትዮጵያ በውክልና ጦርነት አትንበረከክም!' የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት አሸባሪዎቹን እያወገዙ ናቸው።
ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመቆምና በግንባር በመሠለፍ አገርን ለማዳን እንደሚዘምቱም ሰልፈኞቹ በያዟቸው መፈክሮች እየገለጹ ናቸው።
አገርን ለማዳን እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻ ባላቸው ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት እንደሚደግፉም በሰልፉ ላይ አስተጋብተዋል።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።