በተደራጀ ህዝብና በፀጥታ ሃይሉ ተጋድሎ የአሸባሪውን ህወሃት ወረራ መመከትና የጥፋት ተልእኮ ማክሸፍ አለብን

141

ጥቅምት 27/2014 (ኢዜአ) በተደራጀ ህዝብና በፀጥታ ሃይሉ ተጋድሎ የአሸባሪውን ህወሃት ወረራ መመከትና የጥፋት ተልእኮ ማክሸፍ አለብን ሲሉ የቀድሞ አየር ኅይል ባልደረባ ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን ኅይሌ ተናገሩ።

ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የተሰነዘሩባትን ውጫዊ ጥቃቶች ለማምከን ተጋደሎ ያደረጉ አርበኞች እንዳሉ ሁሉ በዘመናዊ የጦር ሰራዊት ታሪኳም ዕልፍ የመከላከያ ጀግኖች አሏት።

የቁርጥ ቀን ጀግኖች በታዩበት በ1969ኙ የዚያድ ባሬ ወረራ አኩሪ ገድል በመፈጸም የኢትዮጵያን ግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ካስከበሩት መካከል የስመ-ጥር ጀግኖች መፍለቂያው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አንዱ ነበር።

አሁን ላይ የ77 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋው ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን ኅይሌ ከጄኔራል ፋንታ በላይ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ፣ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህና መሰል ጀግኖች ጋር ጠላትን ከተዋጉ የአየር ኅይል ባልደረቦች መካከል አንዱ ነበሩ።

ከወታደር ቤተሰብ የተወለዱት የካምቤራ ተዋጊ አውሮፕላን አብራሪው ጄኔራል መስፍን ሃይሌ በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ አገር ደደር የተወለዱ ሲሆን በሀረር መድሀኔአለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል።

በልጅነታቸው የአየር ሃይል ትምህርት ቤትን የተቀላቀሉት ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን በወቅቱ ትምህርት ቤቱን ከተቀላቀሉ 43 ተማሪዎች መካከል የትምህርቱን ክብደት ተቋቁመው ከተመረቁ 11 ተማሪዎች አንዱ  ናቸው።

በ1960 ዓ.ም በአየር ሃይል የመቶ አለቃ መእረግተኛ በመሆን የተመረቁት ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን ሃይሌ ካንቤራ የተሰኘውን የአሜሪካ ሰራሽ ተዋጊ አውሮፕላን ይዘው ቆይተው፤ ከ1969 እስከ 1971 ዓ.ም  የሶማሊያን ተዋጊ አውሮፕላኖች በተለያዩ ግንባሮች ካመከኑ ንስሮች አንዱ ናቸው።

በእንግሊዝ እና በሩስያ የአየር ሃይል ውጊያ ትምህርቶችን የወሰዱት ጄኔራል መስፍን ካንቤራን ብቻ ሳይሆን ኤፍ-ፋይቭ እና ሚግ-23 የውጊያ አውሮፕላኖችንም በማብራር በምስራቅና ሰሜን ኢትዮጵያ ጠላትን ተዋግተዋል።

በኦጋዴን ውጊያ ላይ ሳሉም ተዋጊ አውሮፕላናቸው በጠላት ተመትቶ በመቃጠሉ ከጓዳቸው ጋር በፓራሹት ወርደው በጠላት እጅ ሳይወድቁ ዳግም ጠላትን ለመግጠም በቅተዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን በተዋጊነት፣ በ3ኛው አየር ሃይል መደብ አዛዥት ከኦጋዴን እስከ ኤርትራ በተለያየ የአዛዥነት ሃላፊነት አገራቸውን በአጠቃላይ ለ34 ዓመታት ያገለገለሉ የጦር መኮንን ናቸው።

በ1983 ዓ.ም ኢትዮጵያ ጠል የሆነው አሸባሪው ህወሃት ወደ ስልጣን መጥቶ የቀድሞ ጦር ሰራዊትን ሲበትን ለአገራቸው ዘብ የቆሙት ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን ለ9 ዓመታት በግፍ ለእስር ተዳርገዋል።

ከግፍ እስራቱ በኋላም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ6 ዓመታት በበረራ አስተማሪነት ስመጥር አብራሪዎችን አፍርተዋል።

በኋላም በደቡብ ሱዳን የግል አቬሽን ኩባንያ አቋቁመው ለሶስት ዓመታት ስለመስራታቸው ጡረተኛው መኮንን ይናገራሉ።

"ለ9 ዓመት የህል አስር ቤት ቆየሁ። ከዛ በኋላ ከአስር ቤት አነደወጣሁ ቤተሰቤን ካረጋጋሁና ቦታ ታ ካስያዝኩ በኋላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በፓልት ትሬኒንግ የበረራ አስተማሪ ሆኘኜወደ 6 ዓመት ሰራሁ።በዛ ቆይታዬሀ ብዙ በአሁን ጊዜ ስመጥር የሆኑ ቦይንግ ትሩፕል ሰቨን እና ኤርባስ 350 ሁሉ የሚበሩ ጥሩ ጥሩ ፓይለቶች ላፈራ ችያለሁ "

ዛሬ ኢትዮጵየ የህልውና አደጋ ሲጋረጥባት ለአገራቸው የበኩላቸውን ሚና ለማበርከት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰው፤ የወቅቱን ችግር ከሕወሃት አፈጣጠር ጋር የጀመረ የሩቅ ዘመን ተንከባላይ ችግር ነው ብለውታል።

ኢትዮጵየን አፈራርሶ ታላቋን ትግራይ ለመመስረት የወጠነው የሽብር ቡድኑ በህዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ባለመቀበልና የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ለመነጠል የሚያደርገው አስነዋሪ ድርጊት ነውም ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ የቀሰቀሰው ጦርነት የትግራይን ህዝብ ወደማያቋርጥ መከራ የሚከት፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትስስር የማይበጅና በአገር ኢኮኖሚ ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ አሳዛኝ ድርጊት ነው ብለዋል።

የቡድኑ አካሄድና ኢ-ሰብዓዊ እርምጃ የኢትዮጵያን ህዝብ ያስቆጣ ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል መስፍን፤ ጦርነቱ በህወሃትና በመከላከያ ብቻ ሳይሆን በህወሃትና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል እንደሆነም ገልጸዋል።

በመሆኑም በተደራጀ ህዝብና በፀጥታ ሃይሉ የጀግንነት ተጋድሎ የአሸባሪውን ህወሃት ወረራ መመከትና የጥፋት ተልእኮ ማክሸፍ አለብን ብለዋል።

የተደራጀ ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው የሚሉት ብርጋደል ጄኔራል መስፍን፤ ለአብነትም ቬትናም ቻይናና መሰል ኮሚኒስት አገራት ህዝባቸውን አደራጅተው በማስታጠቅ ውስጣዊና ውጫዊ ጠላትን አሸንፈዋል ብለዋል።

ማዕከላዊ መንግስቱ ለነገ ይደር ሳይባል ህዝብ የማደራጀትና የማንቀሳቀስ ተግባር መፈጸም አለበት፤ የጦርነቱ ባለቤት ህዝብ ነው ብለዋል።

የህዝብ መደራጅት ማህበራዊ መስተጋብር ለመፍጥርና አብሮ ለመቆም እንደሚያስችለው ገልፀው፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት በዚህ ጊዜ ህዝብን አደራጅቶ ለወረራው ምላሽ መስጠት ወሳኝ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን "ልበትናት" ብሎ ከሌሎች ጣላቶች ጋር አብሮ የተነሳ ካሃዲ ሃይል መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም