በመቀበር ላይ የሚገኘውን አሸባሪ ለማዳን የሚደረግ የኤምባሲዎች ውዥንብር! - ኢዜአ አማርኛ
በመቀበር ላይ የሚገኘውን አሸባሪ ለማዳን የሚደረግ የኤምባሲዎች ውዥንብር!
ጥቅምት 27 /2014 (ኢዜአ) አሸባሪውና ወራሪው ህወሓት በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እየተቀበረ መሆኑን ተከትሎ የሽብር ቡድኑን ቀቢጸ ተስፋ ለመመለስ አለም አቀፍ ተቋማትና አንዳንድ ኤምባሲዎች ‘የጸጥታ ችግር አለ’ በሚል ውዥንብር እየፈጠሩ ነው።
ለድርድር ቀርቶ ቅጽበታዊ የተስፋ እስትንፋስ የሌለውን አሸባሪ ቡድን ወደ ስልጣን ለመመለስ አለም አቀፍ አጋሮቹና በእናንተ ጉዳይ እንወስንላችሁ የሚሉ የምዕራባውያን ተዋካዮችም የመረጃ ውዥንብሩ ፈጣሪ አካላት ናቸው።
የውዥንበሩ መነሻ መንግስት የወሰነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና በተባበረ ክንድ የተጠራው የኢትዮጵያውያንን የክተት ዘመቻ ሲሆን በዚህ ሂደት እነሱ የሚፈልጓትን የተዳከመች ኢትዮጵያ ለማየት እንደማያስችላቸው ስላወቁ ወደ መቃብሩ እየተሸኘ ያለውን አሸባሪ ለመመለስ ጥረዋል።
የአሸባሪው የጥቅም አጋሮች ያሏቸውን የትኛውንም የውዥንብር መንገድ ቢጠቀሙ የኢትዮጵያ ክንድ ግን ጠላቱን ከመቅብር አይመለስም።
የሽብር ቡድኑ የጡት አባቶች አሸባሪውን ከሞት አፋፍ ለመመለስ የሚያደርጉትን በውዥንብር የታጀበ ጫና ርብርብ ኢትጵያውያን እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆነው በየዘርፉ እያጠፉት ነው።
ዘማች ክንዶች ደግሞ አሸባሪውን ወደ መቃብር በመሸኘት የኢትዮጵያን ብሩህ ቀን ለማብሰር እንደ ንብ ያለመታከት እየሰሩ ይገኛል።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።