የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

88

ድሬዳዋ ጥቅምት 26/2014 (ኢዜአ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ነገ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።

የዩኒቨርስቲው አለምአቀፍ ና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተናገሩ፤ዩኒቨርሲቲው ለ13ኛ ጊዜ  ከሚስመርቃቸው ተማሪዎች መካከል ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

የዩኒቨርስቲው አለምአቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጋንፉሬ ለኢዜአ  እንደገለጹት  ዩኒቨርሲቲው በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን  3ሺህ 559 ተማሪዎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ነገ ያስመርቃል ።

"በተለያዩ የትምህርት መስኮች ነገ ከሚመረቁት ተማሪዎች  መካከል 1ሺህ 6ቱ ሴቶች ናቸው" ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ነገ በሚካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ስነ ስርአት  ላይ የፌደራልና የድሬዳዋ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሙሩቃን ቤተሰቦች እንደሚታደሙ ከመርሀ ግበሩ ለማወቅ ተችላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም