የጋምቤላና ድሬዳዋ ነዋሪዎች አሸባሪዎቹን ህውሃትና ሸኔን በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላና ድሬዳዋ ነዋሪዎች አሸባሪዎቹን ህውሃትና ሸኔን በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው
ጋምቤላ/ድሬዳዋ ፤ ጥቅምት 26/2014 (ኢዜአ) የጋምቤላና ድሬዳዋ ከተሞች ነዋሪዎች ሀገርን ለማፍረስ እየተጣሩ እየደከሙ ያሉትን የህወሃትና ሸኔን አሸባሪ ቡድኖች በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ነዋሪዎቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ለሀገር ነፃነትና ብልጽግና ዋስትና ነው፣ አሸባሪዎቹ ህውሃትና ሸኔ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው የሚሉ መፈክሮችን በየከተሞቹ ጎዳናዎች እያሰሙ ይገኛሉ።
ከጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆምና በግንባር በመሠለፍ ሀገርን ለማዳን እንደሚዘምቱም አስታውቀዋል።
በሰልፉ ላይ ተማሪዎች ፣ስፖርተኞች ፣የመንግስት ሠራተኞች እና በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆናቸውን የኢዜአ ሪፖርተሮች ከጋምቤላና ድሬዳዋ ዘግበዋል።