የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ ተላላኪዎችን ለማስወገድ ከመቼውን ጊዜ በላይ በአንድነት ቆማናል - ኢዜአ አማርኛ
የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ ተላላኪዎችን ለማስወገድ ከመቼውን ጊዜ በላይ በአንድነት ቆማናል
አዳማ፤ ጅማ፣ ጎባ፣ ሻሸመኔ ፤ጥቅምት 26/2014 (ኢዜአ) አካባቢያቸውን ነቅተው በመጠበቅ የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ ተላላኪዎችን ለማስወገድ ከመቼውን ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆም እንደሚታገሉ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
አሸባሪዎቹን በመቃወም ነዋሪዎቹ በከተማዋ እያካሄዱ ባሉት ሰላማዊ ሰልፍ አሸባሪው ህወሃት ባለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲስራ የነበረ አፍራሽ ፣ዘራፊና ሀገር ለመበተን የተነሳ ቡድን በመሆኑ ቀብሩን ለማሳጠር በአንድነት መቆማቸውን አስታውቀዋል።
ወያኔ ባለፉት 27 ዓመታት የፈፀመብንን ግፍ አንረሳውም፣ እኔ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ፣ ክብር ለጀግኖቻችን፣ ጁንታው ይፈርሳል እንጂ ሀገራችን አትፈርስም የሚሉት መልዕክቶችን ነዋሪዎቹ እያስተላለፉ ነው።
አሸባሪው ህወሃት ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨት የነበረውን ወንድማማችነትና አብሮነትን የሸረሸረ አፍራሽ ቡድን ነው ብለዋል።
አሸባሪው ህወሃትና ተላላኪውን ሸኔ ለማስወገድ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆም እንደሚታገሉ ገልጸዋል።
መከላከያን በሰው ሃይል፣ በገንዘብ፣ በዕውቀት ማገዝና ሞራል መሆን አለብን ሲሉም አመልክተዋል ።
ሰልፉ በተመሳሳይ በጅማ ፣ ሻሸመኔ ፣ በባሌ ሮቤ ፣ በምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌና ሌሎችም የአሮሚያ አካባቢዎች እየተካሄደ መሆኑን ሪፖርተሮቻችን ከየሥፍራው ዘግበዋል።