ቀጥታ፡

አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የፈፀመበት 1ኛ ዓመት መታሰቢይ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

ጥቅምት 24ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የፈጸመበት  አንደኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
በመከላከያ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ እየተካሄ በሚገኘው መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እና ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ሌተናል ጀነራል አበባው ታደሰ፣ ሌሎች የሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖችና አባላት ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ አሸባሪው ህወሃት በሰሜን አዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃትና የአገር ክህደት በማስታወስ በተለያዩ ፕሮግራሞች ይዘከራል።

የአገር መከላከያ ሰሜን እዝ በአሸባሪው ህወሃት ጥቃት የተፈፀመበት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም