የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው የመከራውን ጊዜ ለማሳጠርና የመፍትሔውን ጊዜ ለማቅረብ ነው

160

ጥቅምት 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው የመከራውን ጊዜ ለማሳጠርና የመፍትሔውን ጊዜ ለማቅረብ ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ይኼ ጊዜ ችግሮች ተደራርበው የመጡበት የፈተና ጊዜ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ፈተናው እስኪያልፍ ሁሉም ሰው መፈተኑ አይቀርም” ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ችግሮቻችን አፋጣኝ መፍትሄ አግኝተው ወደ መደበኛ ኑሮ እስክንመስ ሁላችንም አኗኗራችንን ለፈተና ጊዜ እንዲስማማ አድርገን መቆየት አለብን ነው ያሉት።

እንደ ሰላሙ ጊዜ ነገሮች አልጋ በአልጋ እንዲሆኑ መጠበቅ የሰላሙን ጊዜ ያርቀዋል እንጂ ፈጽሞ አያቀርበውም።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀውም የመከራውን ጊዜ ለማሳጠርና የመፍትሔውን ጊዜ ለማቅረብ ነው ብለዋል። ስለዚህ ዜጎች ወቅቱ እንደሚጠይቀው በመሆን፣ አዋጁ የሚያዝዛቸውን መመሪያዎች በማክበር፣ የሕግ አስከባሪ አካላት ሥራቸውን በቅልጥፍና እንዲያከናውኑ በመተባበር እና አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ሁሉም የበኩሉም ሚና እንዲወጣ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም