ቀጥታ፡

ኢግዚቢሽኑ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልከውን የቡና አቅርቦት እንድትጨምር ያግዛል

ጥቅምት 23/2014(ኢዜአ) በቻይና የሚዘጋጀው አራተኛው አለምአቀፍ የገቢ ኤክስፖ የኢትዮጵያ ቡና በቻይና የተሻለ ገበያ እንዲኖረው እንደሚያደርግ ተገለጸ።

ኤክስፖው እኤአ ከህዳር 5 እስከ 10/2021 በሻንጋይ የሚካሄድ ሲሆን በአለም ዙሪያ ያሉ ካምፓኒዎች ምርቶቻቸውን፣ የንግድ ምልክቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና የንግድ አጋሮች የሚገናኙበት እንደሆነ ታውቋል፡፡

የቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ለዥንዋ እንደተናገሩት ኤክሰፖው በኢትዮጵያ ላኪዎችና በቻይና ቡና ገዢዎች መሃከል ትስስርን በመፍጠር የቡና ገበያን ይጨምራል፡፡

ቻይና የኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻ እንደመሆኗ በኤክስፖው ተጨማሪ የንግድ ስምምነቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ኢትዮጵያ ቀደም ሲልም ከኮቪድ-19 በፊት በኤክስፖው ተሳትፋ እንደነበር ዳይሬክተሩ አስታውሰው ለአራተኛው ኤክስፖም የተሳታፊ ላኪዎች ምዝገባ ተካሄዷል።

ዳይሬክተሩ እንዳሉት የኢትዮጵያ ቡና በአይነቱና በጣእሙ ጥራት ያለው በመሆኑ ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ ያደርጋል ፡፡

ቻይና ከቀዳሚ 10 የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻዎች ሃገራት አንዷናት ፤ እንደ ኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን መረጃ እኤአ በ2020/2021 በጀት አመት ኢትዮጵያ 248 ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ 906 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡

ጠብቅ፣ ዝመት፣ ደግፍ

-አካባቢህን ጠብቅ

-ወደ ግንባር ዝመት

-መከላከያን ደግፍ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም