ቀጥታ፡

የኪነጥበብ ባለሙያዎችና የአገር ፍቅር ስሜታቸው

በየትኛውም አጋጣሚ ከፊት ተሰላፊ ናቸው። ደስታንም ይሁን ሀዘንን ተጋርተው ማድመቅና ማጽናናት ይችሉበታል፤ የኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች።

ድምጻውያን በየሙዚቃዎቻቸው መካከል ''ኢትዮጵያ'' የምትለውን ቃል ሳያነሱ ቢያልፉ እርግማን እስኪመስላቸው።

''ኢትዮጵያ'' የአፍሪካ መዲናና የጥንት አባቶችን ታሪክ እያወሱ ኢትዮጵያ ለጠላቶቿ የማትበገር መሆኗን በትውልዱ ልብ ውስጥ እንዲቀር ያደረጉ ባለታሪክ ናቸው።

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተነሳውን አሸባሪውን ህወሓት ከሙያቸው ባሻገር ግንባር ድረስ ሄዶ ለመፋለም ባለማመንት ትውልድ የሚመሰክረው ታሪክ አኑረዋል።

ለአገራዊ ጉዳዮችም ፈጣን ምላሽ በመስጠት ብዙ ሰርተዋል፤ እየሰሩም ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት መንግስት እያከናወነ የሚገኘውንም የህልውና ዘመቻ ለመደገፍና የአገር መከላከያ ሰራዊቱን አለንላችሁ፤ ከጎናችሁ ነን ለማለት ተሰብስበው በልምምድ ረጅም ጊዜን አሳልፈዋል።

በቅርቡ በወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ የሚገኙ ምልምል ወታደሮችን ለማነቃቃት ሲጓዙ ደስ በሚል ጨዋታና ግራ መጋባት ስሜት ታጅበው ጉዞአቸውን እንዳደረጉ ከያኒያኑ ያስታውሳሉ።

ከያኒያኑ ይህንን ጉዞ ሲያደርጉ ወደየት እንደሚያቀኑ ያልተነገራቸው ቢሆንም ከመዳረሻቸው ሲደርሱ ግን ከፍተኛ መደነቅ ውስጣቸው ተፈጥሮ ነበር።

በእንዲህ መልኩ ጉዞአቸውን ካደረጉ በኋላ አዳማንና መተሃራን አልፈው ድሬዳዋንም ወደኋላ አስቀርተው ሁርሶ ኮንቲንጀንት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ደረሱ። እዚያ የነበረው ስሜት ግን በጣም ልዩ እንደነበር የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

በአገር ፍቅር ስሜት በደስታና በዕንባ ታጅበው በወታደሩ ልብ ውስጥ የማይጠፋ ታሪክ አኑረው የተመለሱት ድምጻውያኑ፤ በአጭር ጊዜ የተፈጠሩ ወታደር ናቸው።

እንዲህ ያለው የጥበብ ስራ በኢትዮጵያ የጦርነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዳለው የሚታወቅ ነው። በታሪኳ ሽንፈትን የማትቀበለው የአፍሪካ ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ በየዘመኑ የሚፈጠሩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በፍቅር እየተቀባበሉ ዛሬም ድሉን ለማፍጠን ከጎኑ ተሰልፈዋል፤ ስለሀገር መች ይተርፋል፤ ማንስ አስችሎት ይቀመጣል?

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ከገጠማት ችግር ለመታደግና ጠላቶቻን ለመመከት ከሙያቸው ባሻገር ግንባር ድረስ በመሄድ ታሪክ የሚሰሩ መሆናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም