ሕዝቡ ያለውን መሣሪያ ይዞ ወደ ግንባር በመሄድ የመንጋ ማዕበሉን በሕዝባዊ ምከታ እንዲከላከል ቅስቀሳ ማድረግ ያስፈልጋል

61

ጥቅምት 20/2014(ኢዜአ) ሕዝቡ ያለውን መሣሪያ ይዞ ወደ ግንባር በመሄድ የመንጋ ማዕበሉን በሕዝባዊ ምከታ እንዲከላከል ቅስቀሳ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ የህወሓት የሽብር ቡድንን የሚመክትበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ የጥፋት ሃይል ዋናው አላማ በዝርፊያ፣ በውድመትና በሽብር ሀገር ማፍረስ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

የጥፋት ቡድኑን መመከት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጫፍ እስከ ጫፍ ትበብርና አንድነት ያስፈልጋልም ብለዋል።

ወራሪውን መንጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማስወገድ ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት ዶክተር ለገሰ፤ የዚህን ወራሪ የሽብር ቡድን አቅምና ምኞት መስበርም ዛሬ ነው በማለት ገልጸዋል።

አሸባሪውን ቡድን ለማጥፋት የሠራዊት፣ የህዝብና የአመራር ባለ ሶስት ማዕዘን ውጊያ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይሄን አውቆ በየተሰማራበት ውጤታማ ሥራ በመስራት፤ አቅም ያለው ደግሞ በግንባር በመሰለፍ አሸባሪው ቡድን መመከት ይገባዋል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም