የፌደራልና ክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሰሜን ሜጫ ወረዳ የሰብልና ፍራፍሬ ልማት እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የፌደራልና ክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሰሜን ሜጫ ወረዳ የሰብልና ፍራፍሬ ልማት እየጎበኙ ነው
ባህር ዳር ፤ ጥቅምት 20/2014(ኢዜአ) የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ የሰብልና ፍራፍሬ ልማት እየጎበኙ ነው።
አመራሮቹ እየጎበኙ ካሉት መካከል በወረዳው እንጉቲ ቀበሌ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም ያለሙት የአቡካዶ አትክልትና የበቆሎ ሰብል ነው።
በቀጣይም በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዛት፣ የቡና ልማት ፣ የስንዴና የጤፍ ጨምሮ የተለያየ የሰብል ልማትን እንደሚገበኝ ይጠበቃል።
በክልሉ በመኸሩ ወቅት በተለያዩ የሰብል ዘር ከተሸፈነው ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ውስጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታሩ በገበያ ተኮር የለማ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ከ131 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።
በጉብኝቱ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የፕላን ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴና እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ናቸው።