ቀጥታ፡

ደሴ ከተማ የወትሮ እንቅስቃሴ ውስጥ ትገኛለች

ጥቅምት 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደሴ ከተማ አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል የጥፋት አይን እንዳረፈባት ሳይሆን የወትሮ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች።

በአሸባሪው የህወሃት ወራሪ ቡድን እና ተላላኪዎቹ የሚዘወሩ የተለያዩ የብዙኃን መገናኛ ዘዴዎች ደሴን፣ ሃይቅንና ውጫሌ ከተሞችን ተቆጣጥረናል በማለት የተለመደ የውሸት ፕሮፖጋንዳቸውን እያስተጋቡ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የውሸት ፕሮፓጋንዳው አሸባሪው ህወሃት ከተሞቹን ለማውደም፣ ለመዝረፍና ለማጎሳቆል ጽኑ መሻት እንዳለው በተለያየ አጋጣሚ ሲገለጽ ቆይቷል።

ኢዜአ በደሴ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ባደረገው ምልከታ የከተማ ነዋሪዎች መደበኛ ሰላማዊ የእለት ተለት እንቅስቃሴቸውን በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።

በከተማ የሚገኙ በርካታ የንግድ ድርጅቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ታክሲዎች፣ የመንግስት ተቋማት እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ስራዎቻቸውን በማካሄድ ተገልጋዮቻቸው በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ።

የከተማዋ ወጣቶችም የከተማቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስቀጠል ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ቅንጅት ፈጥረው በቁርጠኝነት እየሰሩ እንደሚገኝ መታዘብ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም