በአሸባሪው ህወሃት የሚለቀቁ ሃሰተኛ መረጃዎችን ህዝቡ እንዳይደናገር እውነቱን ለማሳወቅ ተነሳስተናል - ኢዜአ አማርኛ
በአሸባሪው ህወሃት የሚለቀቁ ሃሰተኛ መረጃዎችን ህዝቡ እንዳይደናገር እውነቱን ለማሳወቅ ተነሳስተናል
ሐረር ፤ ጥቅምት18/2014(ኢዜአ) በአሸባሪው ህውሃት የሚለቀቁ ሃሰተኛ መረጃዎች ህዝቡ እንዳይደናገር እውነቱን በማሳወቅ የድርሻቸውን ለመወጣት መነሳታቸውን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና ሐረር ከተማ ማህበረሰብ ክፍሎች ተናገሩ።
በቡድን የሚሰራጩት ሃሰተኛ መረጃዎችን የመታገሉ ተግባር እንደሆነ ነው የገለጹት።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አመራር እና አስተዳደር ሰራተኛ አቶ ብርሃኑ ስንታየው ፤አሸባሪው የህወሃት ቡድን የሚለቃቸው ሃሰተኛ መረጃዎች አሁን ሳይሆን ቀድሜም አውቃቸዋለሁ ነው ያሉት ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት።
ይህንንም በተለያዩ መረጃዎች በማጣራት ሐሰት መሆኑን እንዳረጋገጡ በመጥቀስ።
በአሁኑ ወቅትም የተማርኩ እንደመሆኔም መጠን በአንድ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎችን በመተንተንና ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን የማረጋገጥ ስራ ስለማከናውን በምንም መንገድ በሃሰተኛ መረጃ አልረበሽም ብሏል።
እኔም በአለሁበት የስራ ቦታ እና በምኖርበት አካባቢ ህዝቡ በሃሰተኛ መረጃዎች እንዳይደናገር እውነቱን የማሳወቅ ስራ እያከናወንኩኝ ሲሉም ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የአራተኛ ዓመት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተመራቂ ተማሪ አረጋ አለሙ በበኩሉ፤ ህብረተሰቡን ላይ ውዥንብር ለመፍጠር እኩይ ተግባር ያላቸው ረ ሰላም ሃይሎች ሃሰተኛ መረጃን እንደሚለቁ ተናግሯል።
ይህንን መከላከል የምችለው በተማርኩበት ሙያ ሳገለግል ብቻ ነው፤እኔም በቅርቡ ወደ ህብረተሰቡ የምቀላቀል ስለሆነ ባለኝ እወቀት በመታገዝ ህዝቡን የማንቃት ስራ በማከናወን የበኩሌን እወጣሉ ነው ያለው።
የሐረር ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ንግስት ኩምሳ፤ በሃሰተኛ መረጃን በፍጹም አልታለልም ሌሎችም እንዳይታለሉ የማስተማር እና የማሳወቅ ስራ እያከናወንኩ እገኛለው ብለዋል።
በተለይ በማያገኟቸው የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም እውነትን የማስረዳት ሰራ እያከናወኑ የበኩላቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ በማመልከት።
የአሸባሪው ህወሃት ፕሮፖጋንዳ ኢትዮዽያን ማፍረስ ነው የሚለው ወጣት እዮብ መኮንን፤ እኔ በበኩሌ እነ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰጡን የተሳሳተ መረጃ አልቀበልም ነው ያለው።
መረጃዎችን ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን በመውሰድ እወነቱን በማረጋገጥ ሌሎችም እንደሚያካፍል ገልጿል።