ቀጥታ፡

የአሸባሪውን ህወሓት ኢትዮጵያን የመበተን ሕልም በማክሸፍ ለዜጎቻችን እፎይታ የምንቸርበት ጊዜ ሩቅ አይደለም

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18/2014 (ኢዜአ) የአሸባሪውን ህወሓት ኢትዮጵያን የመበተን ሕልም በአጠረ ጊዜ በማክሸፍ ለዜጎቻችን እፎይታ የምንቸርበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉ ወሎ ግንባር የተገኙ የጎንደር ፋኖ አባላት ተናገሩ።

ፋኖዎቹ ኢትዮጵያን ክዶ ሕዝቧን ለስቃይ እየዳረገ ያለውን የአሸባሪውን ቡድን ወራሪ ኃይል አከርካሪ ሰብረን ለመደምሰስ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል በገባባቸው የወሎ አካባቢዎች በንፁኃን ዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባራትን መፈጸሙ እንዳስቆጫቸው ገልጸዋል።

ይህን የጭካኔ ተግባርና ወረራ ለማክሰም እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት እንደሚታገሉም አረጋግጠዋል።

ወራሪው አሸባሪ ቡድን ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጥላቻ እንስሳቱን በመግደል፣ ሴቶችን በመድፈር፣ ወጣቶችን በመግደል፣ ቤተ እምነቶችና መሰረተ ልማቶችን በማውደም ዜጎችን ለጉስቁልና መዳረጉንም ተናግረዋል።

በመሆኑም የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ጉዞ ማክተሚያና የመቀበሪያው  ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።

የወሎና አካባቢዋ ማኅበረሰብ ወራሪውን ኃይል ለማጥፋት በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ሠራዊት እያደረገ ያለውን የስንቅና ትጥቅ ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የፋኖ አባላቱ ደሴ ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም