በግንባር ለሚዋደቀው ሰራዊት ደጀንነታችንን ከማጠናከር በተጓዳኝ አከባቢያችንን በንቃት እንጠብቃለን - ኢዜአ አማርኛ
በግንባር ለሚዋደቀው ሰራዊት ደጀንነታችንን ከማጠናከር በተጓዳኝ አከባቢያችንን በንቃት እንጠብቃለን
ዲላ፤ጥቅምት 18/2014 (ኢዜአ) ለአሽባሪው ህውሓት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ጆሮ ሳይሰጡ በግንባር ለሚዋደቀው ሰራዊት ደጀንነታቸውን እንደሚያጠናክሩና አከባቢያቸውን እንደሚጠብቁ የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ከነዋሪዎች መካከል አቶ ዮሴፍ ጉሚ ለኢዜአ እንደገለጹት ''የህወሓት የሽብር ቡድን በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎችና በንብረት ላይ የሚያደርሰው ጥቃት የሁላችንም ጉዳት ነው።
ሰርጎ ገቦችንና የሽብር ቡድኑን የሀሰት ፖሮፓጋንዳ የሚያስተጋቡ አካላትን በንቃት ከመከላከል ባለፈ የህልውና ትግሉ የተራዘመ ጊዜ እንዳይወስድ የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
የጋራ ጠላት የሆነውን የሽብር ቡድን በተባበረ ክንድ ከመመከት ባለፈ በተሰማሩበት የስራ መስክ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል።
ሀገርን ከብተናና ከብዝበዛ ለመታደግ በህልውና ዘመቻው በግንባር ለሚዋደቀው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።
አሸባሪው ቡድን የሀሰት መረጃ ማሰራጨት ባህሪው መሆኑን ያመለከቱት ነዋሪው ለሽብር ቡድኑ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ጆሮ መስጠት እንደማይገባ አመልክተዋል።
እውነተኛ መረጃን ከታማኝ ምንጮች መከታተል እንደሚገባ ጠቁመው የጠላትን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ተቀብሎ ማስተጋባት እንደማይገባ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት በማድረግ የሀገሪቱን ችግሮች ለማቃለል ማቀዱ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ አሸናፍ ማሞ ናቸው
ይሁንና አሸባሪው ህውሓት ዛሬም የሚያስበው በእሱ ቁጥጥር ስር ያለች ኢትዮጵያን በመሆኑ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርገውን ጭፍጨፋና ንብረት ማውደም አጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል።
''በአማራና አፋር ክልሎች የጥፋት ግብሩን ከመፈጸም ባለፈ ይሄንን ያዝኩ፤ ያንን ተቆጣጠርኩ በሚል ቅዠቱ የትግራይ ህዝብን ከማስጨረሱ ባለፈ ሀገር ለማተራመስ እየተጋ ነው'' ብለዋል።
የህውሓት የሽበር ቡድን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ባህሪው በመሆኑ ጆሮ እንዳማይሰጡት ገልጸው አከባቢያቸውን ከተላላኪው ሸኔና ከህውሓት ርዝራዦች በንቃት እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል።
ሌላዋ የዲላ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ዘመናይ ህሪባዬ በበኩላቸው በግንባር ለሚዋደቀው የመከላከያ ሰራዊት ደጀንነታቸውን ከማጠናከር ጎን ለጎን አከባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
አሽባሪው ህውሓት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ባህሪው በመሆኑ ጆሮ እንደማይሰጡት አስታውቀዋል።
የሽብር ቡድኑ ሀገርን ማፍረስን ዓላማ አድርጎ መነሳቱን በሚፈጽማቸው ጥፋቶች ማሳየቱን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።