የቦስተን ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሃት ጥቃት ለተፈናቀሉ 117 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
የቦስተን ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሃት ጥቃት ለተፈናቀሉ 117 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረጉ
ጥቅምት 17/2014 (ኢዜአ) በቦስተን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሃት ጥቃት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ የሚውል ከ117 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አደረጉ ::
በአሜሪካ ቦስተን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በህወሃት ጥቃት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ የሚውል ከ117,000 (አንድ መቶ አስራ ሰባት ሺህ) በላይ የአሜሪካን ዶላር ለግሰዋል::
አዘጋጁን የቦስተን ታስክ ፎርስ፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ለጋሾችንም አመስግነዋል።
ለወገን ደራሹ ወገን ነው በሚል በሌሎች ስቴቶችም ተመሳሳይ ዝግጅቶች እየቀጠሉ መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል::