የምዕራባውያን ሚድያዎች አድሎዓዊ ዘገባ የአሸባሪው ህወሃት ድምጽ መሆናቸው ማሳያ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የምዕራባውያን ሚድያዎች አድሎዓዊ ዘገባ የአሸባሪው ህወሃት ድምጽ መሆናቸው ማሳያ ነው
ጥቅምት 17/2014 (ኢዜአ) የምዕራባውያን ሚድያዎች አድሎዓዊ ዘገባ የአሸባሪው ህወሃት ድምጽ መሆናቸው ማሳያ ነው ስትል የሲቢኤስዋጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ገለጸች።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ''ፖሊቲካል ሚስፊትስ'' በተሰኘው የሬድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርባ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጠችው ማብራሪያ የምዕራባውያን ሚድያዎችን ለአንድ ወገን ያደላ ዘገባ ተችታለች።
አሸባሪው ህወሃት በጎረቤት ክልሎች ላይ ግልጽ ጦርነት በመክፈት የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ፤ንብረት እያወደመ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንቅስቃሴን አደናቅፏል ነው ያለችው።ነገር ግን እንደ ኒውዮርክ ታይምስ የመሳሰሉ ምዕራባውያን ሚድያዎች አሸባሪው ቡድን የሚፈጽማቸውን እኩይ ተግባራት ችላ በማለት፤ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ረሃብ እንዲከሰት አድርጓል ሲሉ ከእውነት የራቁ ዘገባዎችን እያሰራጩ መሆኑን ገልጻለች።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ክልሉ የገቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎችን ለጦርነት ተልዕኮ በማዋል እራሱ የትግራይ ህዝብ ችግር መሆኑን አሳይቷል ነው ያለችው።በመሆኑም የምዕራባውያን ሚድያዎች መሬት ያሉ ተጨባጭ እውነታዎችን ወደጎን በመተው የአሸባሪው ህወሃት ድምጽ ሆነው ቀጥለዋል።
ሲኤንኤንም በቅርቡ በትግራይ ክልል ረሃብ ተከስቷል በማለት ምስል አስደግፎ ያወጣው ዘገባ ከህወሃት አክቲቪስቶች እና ደጋፊዎች ያገኘው የተሳሳተ መረጃ እንጂ የክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ገላጭ አለመሆኑን ጠቁማለች።
በመሆኑም የትግራይ ክልል ህዝብ በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ቡድን በሚያደርስበት ዘርፈ ብዙ በደል እና ጭቆና የታፈነ እውነተኛ ድምጹን ማሰማት አልቻለም ብላለች።