ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአጎዋ ተጠቃሚነቷ እንድትቀጥል ተጠየቀ

አዲስ አበባ ጥቅምት 17/2014 (ኢዜአ)  ኢትዮጵያ በአጎዋ የገበያ አማራጭ ተጠቃሚነቷ እንድትቀጥል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጠየቀ።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረጥ ነጻ እድል (አጎዋ) ተጠቃሚነት የተለመደ ድጋፍ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የንግድ ተወካይ ሚስ ያሴዌ ፓይ ጋር ውይይት አድርገዋል።

አጎዋ (AGOA) የአፍሪካ አገራት ምርታቸውን ከቀረጥና ኮታ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲያስገቡ የሚረዳው ስምምነት ሲሆን ከእ.አ.አ 2002 ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡

በአሜሪካ የሚገኙ አንዳንድ አግባቢ ድርጅቶች(ሎቢስቶች) "መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ነው" በሚል የተሳሳተ መረጃ  በማስተጋባት ኢትዮጵያ ከአጎዋ እንድትወጣ ግፊት እያደረጉ  ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒ በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ በተጠቃሚነቷ እንድቀጥል ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም