ቀጥታ፡

በመቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ማሠልጠኛ ተቋም በአየር ኃይል ተመታ

ጥቅምት 16/2014(ኢዜአ) በመቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ማሠልጠኛ ተቋም ዛሬ በአየር ኃይል መመታቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ዛሬ የተመታው ማሰልጠኛ ተቋም በአሁኑ ወቅት በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እየሰለጠኑበት ያለ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም