ቀጥታ፡

አሸባሪውን ህወሓት እየደመሰሰ ለሚገኘው ሠራዊት ደጀንነታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2014 (ኢዜአ)የአማራ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበርና ደሴ ከተማ የሚገኙ 12 የመረዳጃ እድሮች የአሸባሪውን ህወሓት ወራሪ ኃይል ለማጥፋት በወሎ ግንባር እየተፋለመ ላለው ሠራዊት ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ድጋፋ አበረከቱ።

ድጋፉ የወራሪውን የህወሓት ሃይል በአጠረ ጊዜ ለመደምሰስ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን ተገልጿል።

ለሕይወቱ ሳይሰስት አሸባሪውን ቡድን ለማጥፋት አኩሪ ተጋድሎ እየፈጸመ ለሚገኘው የጸጥታ ኃይል የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተገለጸው።

የአማራ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ስራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አያሌው፤ ማኅበሩ ለሠራዊቱ ያለውን ደጀንነት ለማረጋገጥ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ጫማ፣ ማብሰያ ብረት ድስት እና ሩዝ ማድረሳቸውን ተናግረዋል።

ከድጋፉ ባሻገር እንደ ሙያ ማኅበር በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል የደረሱ ውድመቶችን በመሰነድ ለሕግ ተጠያቂነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በደሴ ከተማ የሚገኙት12 መረዳጃ እድሮች ድጋፍ አስተባባሪ አቶ ዘርይሁን ማንደፍሮም ድጋፉን አሸባሪውን ቡድን እየደመሰሰ ለሚገኘው ሠራዊት ደጀንነታቸውን ለመግለጽ በግንባር ማድረሳቸውን ተናግረዋል።

የደሴ ከተማ ነዋሪ ወራሪው ኃይል ተደምስሶ ግብዓተ መሬቱ እስከሚፈጸም ድረስ ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ በማጠናከር ደጀንነቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በወሎ ግንባር የሚገኙ የሠራዊት አባላት በበኩላቸው የኅብረተሰቡ የደጀንነት ድጋፋ ለበለጠ ድል እንደሚያነሳሳቸው ተናግረዋል።

የሕዝቡ ሁለንተናዊ የደጀንነት ድጋፍ በቀጣይም እንደማይለያቸው እምነታቸው እንደሆነም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም